- Details
- Kategorie: Deforestation
Old-News: 09/20/05
Ethiopian lions eat 20 people, injure 10 others
ADDIS ABABA (Reuters) - Lions disturbed by deforestation have killed 20 people and devoured 750 of their domestic animals in Ethiopia, a local news agency said on Tuesday.
The rare daylight attacks, all during August and in the remote south, have forced a thousand peasant farmers to flee their homes and sparked a hunt for the lions, local official Tadesse Gichore told Walta Information Service.
"The lions killed shepherds tending cattle and villagers after breaking into their houses," Tadesse said of the attacks near his Soro district some 500 km (300 miles) south of the Ethiopian capital Addis Ababa.
"Thousands of people who felt threatened left their abodes and fled to safe areas after the lions killed 20 persons as well as 750 domestic animals last month."
Authorities were hunting the lions, who began roaming after deforestation disrupted their habitat and caused drought along the Gibe River Valley, Tadesse said.
Source:
Reuters
የአንበሳ መንጋ 20 ሰዎችን ፈጀ
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በሃዲያ ዞን የአንበሳ መንጋ 20 ሰዎችን መብላቱንና 10 ሰዎችን ማቁሰሉን እንዲሁም 70 ከብቶችን መብላቱን የአካባቢው ነዋሪዎች የጠቀሱ ዘገባዎች አመልክተውል።
በዘገባዎቹ መሠረት የአንበሳው ጥቃት የደረሰው በሃዲያ ዞን ሲሆን ከአንድ ሺ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ነፍሳቸውን ለማስመለጥ ቄያቸውን ጥለው ጠፍተዋል።
ከአካባቢው ነዋሪዎች ለማወቅ እንደተቻለው አንበሶች አልፎ አልፎ ከቆላም የዞኑ ቦታዎች ወደ ደጋ በመውጣት እንሰሳት ላይ ጥቃት ያደርሱ የነበረ ሲሆን አሁን ሰዎችን መብላት የጀመሩት ደን በመራቆቱና የዱር አራዊት ቁጥር በከፍተኛ መጠን በመቀነሱ አንበሶች ተርበው ነው።
በተለይ ሰዎችን ገድለው መብላት የለመደው የአንበሶች መንጋ ያረጁ አንበሶች የተሰበሰቡበት ሲሆን ይኼውም ከአራዊቶች ይልቅ የሰው ልጆች በቀላሉ መያዝ ስለሚችሉ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል ተብሏል።
ባለፈው ሳምንት በአንበሶቹ የተበሉት እነዚህ 20 ሰዎች በቤታቸውና በቤት አቅራቢያ ሥራቸው ላይ እያሉ መሆኑን ዘገባዎቹ አመልክተው የአንበሶቹን ጥቃት ለመቀነስ አንበሶቹን በመግደል ቁጥራቸው እንዲወርድ ማድረግ አማራጭ የሌለው ዘዴ መሆኑን አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ከጦማር መስከረም 11 ቀን 1998